በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተከፈተ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤ሰኔ 05/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች 8ኛ ቅርንጫፉን መክፈቱ ተገለፀ። በምርቃት ስነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በክብር እንግድነት በተገኙበት እንዲሁም የመንግሥት ከፍተኛ አመራር አካላት፣ሃገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው በተገኙበት የቅርንጫፉን መከፈት አብስሯል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች መመሪያ በጅግጅጋ ከተማ መከፈቱ በክልሉ ለሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር ለክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች የትውልድ ካርድ መስጠትና ማደስ ብሎም ለውጭ ሃገር ዜጎች የኦንላይን ቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠትና ለማራዘም ወደ መዲናችን አዲስ አበባ ሳያመሩ በዚሁ በክልሉ ቅርንጫፍ ማግኘት እንደሚችሉ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉደዮችመምሪያ  ዋና ዳይሬክተር አቶ ገ/ዮሐንስ በመግለፅ በእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑትን የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር መልዕክታቸውን እንዲያስተላልፉ ጋብዘዋል።

"ለኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ይህ ዕለት ትልቅ ታሪካዊ ቀን ነው። የኢትዮጵያን መብት የሆነውን ይህን ፓስፖርት ለማግኘት እጅግ በጣም ረጅምና አድካሚ ጉዞ ካደረጉ ወይንም ከብዙ ችግር በኋላ ነበር ሲያገኙ የነበረው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብም ልክ እንደ ማንኛውም የሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች ወይም ህዝብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ፓስፖርት በመታወቂያው ማግኘት መብትና ግዴታው ነው ሆኖም ግን ለምሳሌ በኢ.ሶ.ክ ከፌርፌር ጅግጅጋ 1500 ኪ.ሜ ነው ከዚህ በተጨማሪም ከፌርፌር እስከ አዲስ አበባ አድካሚ ጉዞ በማድረግ ነበር ፓስፖርት ለማውጣት ይሄዱ የነበረው። በዛ ውስጥ ብዙ ችግሮች ነበሩ ለምሳሌ ሃጂና ኡምራ ለማግኘት አንድ አርብቶ አደር ያውም ጫካ የሚኖር የሐይማኖት ግዴታውን ለመወጣት ሲል የግድ ወደ ሃጅ መሄድ አለበት ፕሮሰሱን በሚጀምርበት ጊዜ ከቀበሌ መታወቂያ ሲያገኝ አንድ አካባቢ ብቻ አዲስ አበባ ሄዶ ነበረ ፓስፖርት ሲያገኝ የነበረው። እንግዲህ እንደሚታወቀው ይህ አርብቶ አደር ወረዳንና ከተማን አይቶ የማያውቅ ሲሆን ከብዙ ውጣ ውረዶች በኋላ አዲስ አበባ ድረስ በመመላለስ ነበረ ፓስፖርት ለማግኘት የሚደርሱት ሌሎች በርካታ ችግሮችም እንደነበሩ ይታወቃል።"

ክቡር ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም "በተለይ ቢሮው ባለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ መሻሻልና ጥሩ ሥራዎች ተሰርተውበት ነበር ምክንያቱም ቀደም ባለው ጊዜ ረጅም ጉዞ ተጉዞ ማግኘትም ጥሩ ነበረ ማለት ይቻላል ከዚህ በፊት ፓስፖርት ፈላጊዎች ተጉዘው ሄደው ላያገኙ የሚችሉባቸውም ጊዜያትም ነበሩ።ነገር ግን በቢሮው ከፍተኛ መሻሻል ስለተደረገ ይሄው ዛሬ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ በጅግጅጋ ከተማ ፓስፖርት የማግኘት መብቱ ስለተረጋገጠ በመጀመሪያ ምሥጋናችንን ለአላህ እናቀርባለን በመቀጠልም ገደብ የሌለው ምሥጋናዬን ለፌዴራል መንግሥትና ለቢሮው አቀርባለሁ። የክልሉን መታወቂያ በዘመናዊ መንገድ የተሠራና በምንም አይነት መልኩ አመሳስሎ (ፎርጅድ) ሊሠራ የማይችል ሲሆን ይሄንን ከቢሮው ጋር ተስማምተን ያደረግነው ሲሆን በተጨማሪም ለሌሎች ክልሎችም ምሳሌ ሊሆን የሚችል አሠራር ነው ክልሉ የዘረጋው” በማለት አብራርተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉደዮች  መምሪያ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገ/ዮሐንስ በበኩላቸው "የጅግጅጋ ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለኢትዮጵያዊያን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪም በተለያዩ የውጪ ሃገራት ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ ለሆኑት የኢትዮጵያ ሶማሌ ልጆች የትውልድ ካርድ የማደስ እና የመስጠት ለውጪ ዜጎች ደግሞ የኦንላይን ቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘትና ለማራዘም አዲስ አበባ ሳይሄዱ እዚሁ ሊየዘገኙ የሚችሉበት ሁኔታ ተመቻችቷል።

 በተመሳሳይ የሃገራችንንና የክልሉን ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ገበያን ለማነቃቃት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ለሚመጡ ተጓዦች ሁሉም ቪዛዎች በኤሌክትሮኒክስ ወይም ኦንላይን ቪዛ መስጠት ተጀምሯል ዋና ዳይሬክተሩ ሲሉ ገልፀዋል።በመጨረሻም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎችም የናሙና ፓስፖርት ከፕሬዝዳንቱ እጅ በመቀበል በይፋ ሥራ መጀመሩን አብስሯል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የእንሰሳትእና ከፊል እርሻ ምርምር ተቋም 132 የቴክኖሎጂ ምርምሮች ማዘጋጀቱን አስታወቀ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)አርብ፤ሰኔ 01/2010 .. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የእንሰሳትና ከፊል እርሻ ምርምር ተቋም በ1994ዓ.ም ከተመሰረተ ጀምሮ የክልሉ አርብቶ አደርና ከፊል አርሶ አደር ኑሮ የሚሻሽል በእንሰሳት፤በሰብል ሀብት ልማት ፣ በግብሪና መካናይዜሽንሽ እንዲሁም ሌሎች ግብሪና የሚያቶክሩ  132 የቴክኖሎጂ ምርምሮች  መከናወኑን አስታውቋል፡፡ ተቋሙ 85 በመቶ የሚሆኑ የክልሉ አርብቶ አደርና ከፍል አርሶ አደር የምግብ ዋስትናና ኢኮኖሚ  ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያከናወናቸው የምርምርና ከህብረተሰብ ጋር  የማላመድ ስራዎችን ለማጠናከር  የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ስሆን ከእስዊዘርላንድ መንግስት ጋር በመተባበርም የዲጂታል የዕፅዋት ናሙና አያያዝና ዝናብ አጠር አከባቢ የሚበቅሉ  ፅዋት ለማላመድና ዚሪያዎችን ለማስፋፋት የሚያስችል ፕሮጄክቶች እያከናወነ ይገኛል፡፡

በክልሉ የሚገኙ በርካታ የዕፅዋት ስብስብ ናሙና በዲጂታል በሆነ መንገድ በመሰብሰብ እና ለማቆየት እንዲሁም በሀገራችን በክልሉ ብቻ የሚገኙና በማጥፋት አደጋ ላይ ያሉ እፅዋቶችዝሪያዎች ለማስፋፋት ተቋሙ የሚያከናወነው  የፖሮጀክት አተገባበር ከትላንትናው ዕለት በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሚስተር ደንኤል የሚመራ ልዑኳን ቡድን በተቋሙ ስራዎች ጎበኝቷል፡፡ልዑካን ቡድኑ የክልሉ መንግስት የእንሰሳት እርባታና ከፊል እርሻ ምርምር ተቋም ሀላፊዎች፣ ተመራማሪዎችና ባላዉዎች በተገኙበት መድረክ በጅጅጋ ከተማ ተገኝተው በፖሮጀክቱ እየተካናወኑ ያለው የዲጂታል የእፅዋት አያያዝን፣የዉብተክል የማላመድና ስርቶ ማሳያ እንዲሁም በተቋሙ ሰርቶ ማሳያ መዓከል እየተከናወኑ የሚገኙ የሰብል ምርምር፣ ማላመድና ቴክኖለጂ ሽግግር ስረዎችን ተዛዋዊሮ የጎብኙ ስሆን በተቀሙ ባላሙዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በጉብኝቱ የተገኙት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የእንሰሳት እርባታና ከፊል እርሻ ምርምር ተቋም ም/ዳይሬክተር አቶ አብዱረህማን መሀመድ እንዳሉን የልዕኳን ቡዲኑ ዋና አላማ በምርምር ላይ የሚገኙ ፕፖሮጀክቶችን ተግባራዊነት ለመመልከት እንደሆነ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም  ም/ዳይሬክተሩ “ዛሬ የመጠው የስዊዘርላንድ አምበሳደርና ከጀአይዜድ የመጣ ዴሊገሽ ናቸው፡፡ የጉብንቱ ዋና አላማ የእኛና ጀኣይዜድ ው የትብብር ስራ እንዲሁም ከጂአይዜድ የወሰድነው ሁለት ፖሮጀክቶች ስላሉ ለመከታተልና ለማየት ነው፡፡እነዚህ  ሁለቱ ፖሮጀክቶች አንዱን ሀርፓሪያን ዲጂታላይዜሽን የሚባል ሲሆን ይህ ሀርፓሪያን ከ20 አመት በፊት በክልላችን የተሰበሰበ ዝርያ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመቀየር ነው በዚህም  ፖሮጀክቱ በጣም ውጤታማ መሆኑን አረጋግጧል። ሀለተኛ ደግሞ ወተር ፖክስ የሚባልና በድርቅና ዉሃ መቆራረጥ በሚኖርበት ወቅት የተለያዩ አትክልት ለመተክል የዝናብ ውሃ ለማጠራቀምና ዉሃን እንዲያዝ የሚንጠቀምበት ነው” ሲሉ ተናግሯል፡፡

በሌላ በኩልም የተቋሙ ተመራማሪዎች በበኩላቸው በፖሮጀክቱ እያተከናወኑ የሚገኙ የዲጂታል  ምርምርና የእፅዋት ናሙና አያያዝ ስራዎች በክልሉ የዝናብ አጠር አከባቢዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና በዘርፉ ለሚከናወኑት የሚርምር ስራዎች የጎላ ጠቀሜታ እነደሚያበረከቱ አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ብቻ የሚገኝና በዓለም ላይ ተወዳጅ የሆነና ይእብ የተባለ እፅዋት ዝሪያ ከአሁን በፊት በአምስት ዞኖች ላይ እንደነበረና በአሁኑ ወቅት ግን  በዶሎ ዞን ስር የሚገኙ አንዳንድ ቀበሌዎች ብቻ እንደሚገኝ እንድሁም የአከባቢው ህብረሰብ ለምግብ ፣ለቤት መስሪያና ለእንሰሳት ምግብነት ስለሚጠቀሙ በስዊዘርላንድና በጂኣይዜድ ድጋፍ የሚሰራ የምርምርና ዲጂታላይዜሽን ፖሮጀክቶች የይእብ እፅዋት ዝሪያዎች ከአደጋ እንደዳነና አሁንም በስጋት እንደሚገኝም ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል።

 

የኢ.ሶ.ክ.አከባቢ ጥበቃ᎓ማዕደን᎓አኔርጂና ደን ልማት ኤጄንሲ ከጅግጅጋ ከተማ መስተዳድር ጋር በመሆን በጅግጅጋ ከተማ የፅዳት ዘመቻ አካሄደ

ጅግጅጋ (Cakaaranews) እሁድ፤ግንቦት 26/2010.. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አከባቢ ጥበቃ᎓ማዕደን᎓አኔርጂና ደን ልማት ኤጄንሲ ሰረተኞች ከጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር  አመራር አካላትና ሰረተኞች ጋር በመተባበር  በክልሉ መንግስትርዕሰ መዲና በሆነችው በጅግጅጋ የአለምአቀፍ የአከባቢጥበቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ በከተማው የፅዳት ዘመቻ ስራ አከናወነዋል፡፡ የፅዳት ዘመቻው በዋነኝነት ጅግጅጋ ከተማንፅዱናአረንጓዴለማድረግእንዲሁምአካባቢንማፅዳትየኅብረተሰቡቋሚተግባር ከማድረግ ጋር የተያያዘ ስራ መሆኑንም ተገልጸዋል፡፡   

በዚህም የፅዳት ዘመቻው ዋና አለማ ጅግጅጋ ከተማንፅዱናአረንጓዴለማድረግ፣ በከተማው ህብረተሰብ ላይ  የሚታየውንየቆሻሻአያያዝጉድለትለመቅረፍ እንዲሁም በቆሻሻምክንያትየሚከሰተውብክለትለአካባቢደህንነትአንዱናዋነኛውአሳሳቢጉዳይመሆኑንና የአከባቢጥበቃናአረንጓዴልማትሥራዎችወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አከባቢ ጥበቃ᎓ማዕደን᎓አኔርጂና ደን ልማት ኤጄንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መውሊድ ሃይር ሀሰን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ዋና ሥራ አስኪያጅጁ በክልል ደረጃ በካራመርዳ ተራራ የተከናወነው የአከባቢ ጥበቃና የፅዳት ቅስቀሳ በአለምአቀፍ የአከባቢጥበቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መርሀ-ግብር መሆኑንም አብራርቷል፡፡     

 በሌላ በኩል የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲአዚዝ መሀድ  ዝግጅቱ ጅግጅጋ ከተማንፅዱናአረንጓዴለማድረግ እንዲሁም ሶዎች በከተማው ውስጥ የሚጣሉት ደረቅ ቁሻሻዎችን ለማስወገድ የታለመ የፅዳት ስራ  ነው ብሏል፡፡በአጠቃለይ በከተማው እየተከናወነ ያለው የፅዳት ቅስቀሳ ተግባራት “ደረቅ ቁሻሻዎችን እንዋጋለን” የሚል መሪ ቃል ተከብረዋል፡፡

 

 

የኢ.ሶ.ክ.መ. የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በመንገድ በማስተሳሰር የማህበረሠቡን ልማት ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ተገለጸ

ቀብሪበየህ(cakaaranews)እሮብ:ግንቦት 29/2010ዓ.ም.በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ከቀብሪበያህ ከተማ አስተዳደር እስከ ሀርቲሼክ እየተሠራ ያለው የኮንክሪት አስፋልት መንገድ በተያዘለት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ። የክልሉን ዞኖችና ወረዳዎችን በመንገድ መስረተ ልማት ለማስተሳሰር ከሚደረገው የልማት ሥራዎች አንዱ የሆነው ከቀብሪበያህ እስከ ሀርቲሼክ ድረስ ያለውን የ23 ኪ.ሜ ርቀት በኮንክሪት አስፋልት መንገድ ለመሸፈን የተጀመረው ሥራ በታቀደለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ የተናገሩት የቀብሪበያህ ሀርቲሼክ መንገድ ፕሮጀክት ኮንስትራክሽን መሃንዲስ አቶ ሳምሶን ገ/አብ ናቸው።

በዚህም አቶ ሳምሶን ገ/አብ "ሁለት ነገሮችን ነው የሠራ ነው ከጠረጋው ሥራ ጎን ለጎን የካምፕ ኮንስትራክሽንም ሥራ ነበረ በዛም ላይ የሁለቱም ጠረጋ ሥራም ሌላው ነው። ሊፈጅብን የሚችለውም ጊዜ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንጨርሳለን ብለን እናምናለን" ሲሉ ገልጿል።

በጨማሪም የመንገዱ መሠራት በአካባቢው የሚገኘውን ማህበረሠብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳደግላቸው የሚታመን ሲሆን የመንገድ ፕሮጀክቱ መጀመርም የሥራ እድል መፍጠር እንደቻለም ኃላፈው ተነግሯል። በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም ሥራው የተጀመረው የቀብሪበያህ ሀርቲሼክ የኮንክሪት አስፋልት መንገድ ሥራው በተጀመረ በአጭር ጊዜያት ውስጥ የ5 ኪ.ሜ የጠረጋ ሥራና የመንገድ ካርታ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀም የኮንስትራክሽን መሃንዲሱ አብራርቷል።

"አሁን የደረስንበት ደረጃ  5 ኪሎሜትርን የቤንች መሙላት ሥራና የአፈር ጠረጋ ሥራ ጨርሰን  በዲዛይኑ መሠረት የሙሌት ሴክሽን ነው የመጀመሪያ ደረጃ ሙሌት በ15 ኪ.ሜ ውስጥ እየሠራን ሲሆን በቀጣይም የ5 ኪ.ሜ ጠረጋ ሥራዎችን እንሠራለን።" ሲሉ አቶ ሳምሶን ተናግሯል።

በርካታ ሥራዎች እንደሠሩ የተናገሩት የፕሮጀክት ኮንስትራክሽን መሃንዲሱ የ23 ኪሎሜትሩ የጥርጊያ መንገድ ከተጠናቀቀ በኋላ አስፋልት የማንጠፍ ሥራ እንደሚጀመርም አስረድቷ። የቀብሪበየህ ሀርቲሼክ የመንገድ ፕሮጀክት አንድ የኮንክሪት አስፋልት  መንገድ ሲሆን የፕሮጀክቱን ኮንትራት የወሰደውን  የኢ.ሶ.ክ. ገዢና ልዩ ኮንስተራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከመሆኑ ባሻገር የክልሉ ዲዛይንና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ በፕሮጀክቱ ኮንስተራክሽን ስራዎች ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግም ተገልጿል።

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከስዊዘርላንድ ጋር በመተባበር የዋን ሄልዝ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀት ይፋ መደረጉ ተገለፀ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅዳሜ፤ግንቦት 25/2010ዓ.ም የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከስዊዘርላንድ መንግሥት ጋር በመተባበር የሚተገብረው ዋን ሄልዝ ኢኒሼቲቭ የተባለ ፕሮጀክት በመጀመሪያ ምዕራፍ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሸበሌ ዞን አዳድሌ ወረዳ የተሠሩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ይፋ አደርገዋል። ለፕሮጀክቱ የተሠሩ የምርምር ሥራዎች በሸበሌ ዞን አዳድሌ ወረዳ ነዋሪዎችና እንስሳቶችን በተቀናጀ ሁኔታ ተጠቃሚ ለማድረግ በሚተገበሩ ስራዎዎች መሆናቸውን በጅግጀጋ ከተማ በተደረገደው የባለድርሻ አካላት ውይይት መድረክ ላይ ለማወቅ ተችሏል።

85 በመቶ አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር ማህበረሠብ በሚኖርበት የኢትዮጵያ ክልል የሚገኘው ጅግጀጋ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመ ጀምሮ ከተለያዩ የሃገር ውስጥና ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ጋር በትብብር እየሠራ ሲሆን ከስዊዘርላንድ የልማት ትብብር ኤጀንሲ ጋር በተደረገ የሶስትዮሽ ስምምነት መሠረት ከሶስት ዓመታት በፊት ዋን ሄልዝ ኢኒሼቲቭ(one health iniative) የተባለ በሃገሪቱ የመጀመሪያ የሆነ ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገም ተገልጿል። ፕሮጀክቱ በመጀመሪያው ምዕራፍ እየተካሄደ ከሚገኘው የአቅም ግንባታ ስራዎች በተጨማሪም በክልሉ ሸበሌ ዞን አዳድሌ ወረዳ ሲከናወኑ የነበሩ አርብቶ አደሮችንና ከፊል አርብቶ አደሮችን ፍላጎትና ችግሮችን መሠረት ያደረጉ የምርምር ሥራዎች ተጠናቀው በትላንትናው ዕለት በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የባለድርሻ አካላት የምክክር አውደ ጥናት ላይ ቀርቧል።

በጅግጀጋ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የአዳድሌን ህብረተሠብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተሠሩ የምርምር ሥራዎች እውቅና መስጫ አውደ ጥናት ላይ የተገኙት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዲአዚዝ ኢብራሂም እንደተናገሩት በስዊዘርላንድ መንግሥት የሚደገፈው ዋን ሄልዝ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት ከአቅም ግንባታ ሥራዎች ጎን ለጎን በክልሉ ሸበሌ ዞን አዳድሌ ወረዳ ህብረተሠቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ከእንስሳ ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል እና በተቀናጀ መንገድ የሰው እና እንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚተገበር ፕሮጀክት መሆኑን አስታውቀዋል።

በተያያዜም ዶ/ር አብዲአዚዝ ስለ ፕሮጀክቱ ገልፃ ሲሰጡም በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ውል የገቡትና ፈንድ የሚያደርገው የስዊዘርላንድ መንግሥት ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የአቅም ግንባታውንም ሆነ ፕሮጀክቱንም ተደራሽ የሚያደርጉት በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በኩል ሲሆን የስዊዘርላንድ መንግሥትና የስዊዘርላንድ ባስ ዩኒቨርሲቲ ናቸው። የሶስትዮሽ ስምምነት ነው ያደረግነው በዚህ የሶስትዮሽ ስምምነት ላይ ለሶሰት ተከታታይ ዓመታት የተሠሩ ሥራዎች ስላሉ ከአቅም ግንባታው ጎን ለጎን ደግሞ ተማሪዎቻችን መጀመሪያም መምህራን ስለነበሩ አቅማቸውን የሚገነቡት ደግሞ በተመረጡ ወረዳዎች ላይ ሲሆን 1ኛው የአዳድሌ ወረዳ ነው። ተማሪዎቻችን አዳድሌ ወረዳ ላይ ባደረጉት ጥናት የምርምር ሥራዎቻቸው ለምርቃት የሚበቁበትን ጥናታዊ ፅሁፎቻቸውንም ይሠሩበታል። ጥናቱ 3 መፍትሄዎችን ነው ያገኘው 1ኛው ንፁህ የመጠጥ ውሃን ለአዳድሌ ወረዳ ህብረተሠብ በዝቅተኛ ወጪ ተደራሽ ማድረግ ነው። 2ኛው ህብረተሠቡ የሣንባ ነቀርሳ በሽታ በሚከሰትበት ወቅት ራሱን እንዴት እንደሚከላከል ግንዛቤ ማስጨበጥ ሲሆን 3ተኛው ደግሞ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚዛመቱ በሽታዎችን በቡድን እየተናበቡ ሪፖርት አጠናቅሮ እንዴት እንደሚሠራ ሪፖርት ማድረግ ናቸው” ብሏል።

በመጨረሻም የጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ ዋን ሄልዝ ኢኒሼቲቭ  ፕሮጀክቱ ለ12 ዓመታት እንደሚቆይ የተገለፀ ሲሆን በአውደ ጥናቱም በአዳድሌ ወረዳ የተሠሩ የጥናትና ምርምር ሥራዎችም ቀርበው በአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

Amharic News 08_09_10


Amharic News 07_09_10


Amharic News 05_09_10Amharic News 04_09_10Amharic News 26_08_10


Amharic News 25_08_10


Amharic News 24_08_10Amharic News 23_08_10Amharic News 22_08_10


Amharic News 21_08_10Amharic News 20_08_10


Amharic News 19_08_10Amharic News 18_08_10


Amharic News 17_08_10